ሳንኮሬ ማድራሣ

ሳንኮሬ ማድራሣ በቲምቡክቱ፣ ማሊ መንግሥት፣ ከ981 እስከ 1585 ዓም ያህል የቆየ የእስልምና መስጊድና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወይም ዩኒቨርሲቲ ነበረ። ከቲምቡክቱ ዩኒቨርሲቲ ሦስት ተቋማት መጀመርያው የተመሠረተው ነበር።

መስጊዱ የተመሠረተው በ981 ዓም በቲምቡክቱ ዳኛ በአል-ቃዲ አቂብ ነበረ። ከ1100 ዓም ያህል በፊት በአንዲት ሀብታም ማንዲንካ ወይዘሮ እርዳታ፣ ሕንጻው ሰፊ ማድራሣ (ተቋም) ሆነ። ያንጊዜ የአውሮፓ ትልቅ ዩኒቨርሲቲዎች ገና ምንም ሳይኖሩ፣ ለአፍሪካ ከፍተኛ ደረጃ ተማሮች ግን የእስላም ማድራሦች በቲምቡክቱ፣ በካይሮ እና በሞሮኮ ተገኝተው ነበር።

በ1200 ዓም ግድም የተማሮች ቁጥር 25,000 ነበር፤ የከተማውም ሕዝብ ቁጥር ያንጊዜ 100,000 ነበር። በተለይ ከ1300 ዓም በኋላ በጣም ስመ ጥሩ ትምህርት ተቋም ሆነ።

የተቋሙ መደበኛ ቋንቋ አረብኛ ነበር። በተማሮች መጀመርያ ዓመት ቁራኑን ሙሉ በአረብኛ ከልብ መዳግም ነበረባቸው። ዋና የጥናት ዘርፎች እስልምና፣ ቁራን፣ ሕግና ሥነ ጽሑፍ ነበሩ። በተጨማሪ ሕክምና፣ ቀዶ ጥገና፣ ሥነ ፈለክ፣ ትምህርተ ሂሳብ፣ የተፈጥሮ ሕግጋት ጥናት፣ የጥንተ ንጥር ጥናት፣ ፍልስፍና፣ የቋንቋ ጥናት፣ መልክዓ ምድር፣ ታሪክና ሥነ ጥበብ ጥናቶች አስተማሩ። ከዚያ በላይ ተማሮች ንግድ ወይም ሙያ ይማሩ ነበር፦ አናጢነት፣ ግብርና፣ አሣ ማጥመድ፣ ግንባታ፣ ጫማ መሥራት፣ ልብስ ሰፊነት፣ ወዘተ. ይማሩ ነበር።

በ1319 ዓም ሁለተኛ ማድራሣ ጂንገሬ በር ተቋም ተሠራ፤ በ1392 ዓም ሦስተኛው ተቋም ሲዲ ያህያ ተሠራ ። እነዚህ ሦስት ማድራሦች፣ ሳንኮሬ፣ ጂንገሬ በር እና ሲዲ ያህያ፣ አንድላይ የቲምቡክቱ ዩኒቨርሲቲ ይባሉ ነበር። በ1460 ዓም ቲምቡክቱ ከማሊ መንግሥት ወደ አዲሱ ሶንግኃይ መንግሥት ዓለፈ። በ1585 ዓም ግን የሞሮኮ ወራሪ ሃያላት ማድራሦቹን አጠፉ፣ ብዙ መጻሕፍት ቤቶችንም አቃጠሉ። ቢሆንም ከማድራሣው 70,000 ያህል ሰነዶች እስካሁን ተርፈዋል፣ ዛሬም እየተነተኑ ነው።

ዝነኛ አስተማሮች፦

  • አህማድ ባባ አል-ማሡፊ (1549-1619 ዓም) የተቋሙ መጨረሻው መሪ፣ 60 መጻሕፍት ጽፈው ነበር። ሞሮካውያን ወደ ስደት ላኩት።
  • ሞሐመድ ባጋዮጎ (1515-1585) ፋላስፋ፣ ጸሐፊና መምህር፣ በሞሮካውያን ተገደለ።
Listed in the following categories:
አስተያየት ለጥፍ
ምክሮች እና ፍንጮች
ለ ሳንኮሬ ማድራሣ ገና ምንም ምክሮች ወይም ፍንጮች የሉም። ምናልባት ለእርስዎ ተጓlersች ጠቃሚ መረጃዎችን ለመለጠፍ እርስዎ የመጀመሪያ ሊሆኑ ይችላሉ? :)
6.5/10
الحسن بشير ثاني እና 1,479 ተጨማሪ ሰዎች እዚህ ተገኝተዋል
Bravia Hotel Ouagadougou

$218 ጀምሮ

Sopatel Silmandé

$180 ጀምሮ

Hotel Splendid Ouagadougou

$123 ጀምሮ

Faso Hotel

$119 ጀምሮ

Hotel Palm Beach

$107 ጀምሮ

Elite Hotel

$35 ጀምሮ

በአቅራቢያ የሚመከሩ ዕይታዎች

ሁሉንም ተመልከት ሁሉንም ተመልከት
የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Timbuktu

Timbuktu (Timbuctoo) (Koyra Chiini: Tumbutu; French: Tombouctou) is a

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Djinguereber Mosque

The Djinguereber Mosque (Masjid) in Timbuktu, Mali is a famous

ተመሳሳይ የቱሪስት መስህቦች

ሁሉንም ተመልከት ሁሉንም ተመልከት
የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
University of Helsinki

The University of Helsinki (Finnish: Helsingin yliopisto, Swedish:

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
University of Tokyo

The University of Tokyo (東京大学, Tōkyō daigaku), abbreviated as Todai

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Sofia University

The St. Clement of Ohrid University of Sofia or Sofia University

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Charité

The Charité - Universitätsmedizin Berlin is the medical school for b

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Ghent University

Ghent University (in Dutch, Universiteit Gent, abbreviated UGent) is

ሁሉንም ተመሳሳይ ቦታዎች ይመልከቱ