ኤብላ

ኤብላ የሶርያ ጥንታዊ ከተማ ነበር። ዛሬው ሥፍራው በአረብኛ ተል ማርዲኽ ተብሎ የኤብላ ጽላቶች የተገኙበት ፍርስራሽ ነው።

ከአካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን አስቀድሞ በሆነው ዘመን ኤብላ ሰፊ መንግሥት በሶርያ ዙሪያ እንደ ነበረው ይታወቃል። የጽላቶች ቤተ መዝገብ ሕንጻ የተቃጠለበት ጊዜ የሚከራከር ነው። ሦስት ዋና አስተያየቶች አሉ፤ 1) ከሳርጎን በፊት በኤብላ ተፎካካሪ በማሪ፤ 2) በሳርጎን እራሱ፤ ወይም 3) በሳርጎን ልጅ ልጅ በናራም-ሲን። አሁን በሳርጎን ዘመን በ2074 ዓክልበ ግድም እንደ ጠፋ ቢመስልም በሳርጎን ወይም በማሪ ሰዎች እጅ መጥፋቱን እርግጠኛ አይደለም።

የኤብላ ጥንታዊ መንግሥት

ኤብላ መቼ እንደ ተመሠረተ ባይታወቅም ምናልባት 2400-2350 ዓክልበ. (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) እንደ ሆነ ሊገመት ይቻላል። የሥነ ቅርስ ሊቃውንት ግን እስከ 3000 ዓክልበ. ድረስ ይገፉታል።

በአንዱ ጽላት ላይ ከኢግሪሽ-ሐላብ (2127 ዓክልበ. ግድም) አስቀድሞ የገዙት ፴ ነገሥታት ስሞች ይዘረዝራሉ፦ ሳኩሜ፣ ሹ-[...]፣ ላዳው፣ አቡጋር፣ ናምነላኑ፣ ዱሙዳር፣ እብላ፣ ኩልባኑ፣ አሻኑ፣ ሳሚዩ፣ ዚያሉ፣ ሩማኑ፣ ናማኑ፣ ዳ-[...]፣ ሳጊሹ፣ ዳኔዩም፣ ኢቢኒ-ሊም፣ ኢሽሩድ-ዳሙ፣ ኢሲዱ፣ ኢሽሩድ-ሐላም፣ ኢክሱድ፣ ሪዳ-ሊም፣ አቡር-ሊም፣ አጉር-ሊም፣ ኢቢ-ዳሙ፣ ባጋ-ዳሙ፣ ኤናር-ዳሙ፣ ኢሻር-ማሊክ፣ ቁም-ዳሙ፣ እና አዱብ-ዳሙ ናቸው።

ከነዚህ ስሞች ብዙ በሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶቻቸው ደግሞ ይገኛሉ፣ በተለይም ከ«ሳጊሹ» እስከ «ኢሽሩድ-ዳሙ»፣ እና «ኤናር-ዳሙ» ያሉት ስሞች ይጠራሉ። ኢቢ-ዳሙ በካነሽ ሐቲ ከተገኘ ማኅተም ቅርስ ይታወቃል። ቁም-ዳሙ ከሌሎች ሰነዶች ሲታወቅ ከማሪ መንግሥት ጋራ የሆኑት ችግሮች በእርሱ ዘመን እንደ ጀመሩ ይመስላል። ይህም በማሪ ነገሥታት ሳዑሙ ወይም ኢቱፕ-ኢቫር ዘመናት እንደ ነበር ይታሥባል። ተከታዩም አዱብ-ዳሙ እጅግ አጭር ዘመን እንደ ነገሠ ይታወቃል።

የተገኙት መዝገቦች ከአዱብ-ዳሙ በኋላ ከገዙት ከሦስቱ መጨረሻ ነገሥታት ዘመኖች ናቸው። እነርሱም ኢግሪሽ-ሐላብ (12 ዓመታት)፣ ኢርካብ-ዳሙ (7 ዓመታት) እና ኢሻር-ዳሙ (35 ዓመታት) ናቸው (2127-2074 ዓክልበ.)። ከሃይለኛ ጠቅላይ ምኒስትሮቻቸው የሚታወቁ አራኩም፣ ኤብሪዩም እና ኢቢ-ዚኪር (ወይም ኢቢ-ሲፒሽ) ናቸው። መዝገቦቹ የተጻፉበት ኩኔይፎርም በተባለ ጽሕፈት ሲሆን ቋንቋቸው ኤብላኛ ነው፣ ይህ ለአካድኛ ተመሳሳይ የሆነ ሴማዊ ቋንቋ ወይም ቀበሌኛ ነው።

ኢሻር -ዳሙ በማሪ ላይ ከናጋርና ከኪሽ ጋራ ስምምነት ተዋዋለ፤ አለቃውም ኢቢ-ዚኪር የማሪን ሃያላት በተርቃ ውግያ አሸነፋቸው። ከዚህ በኋላ የኤብላ ሥራዊት አርሚን ያዙ፣ የኢቢ-ዚኪርም ልጅ ኤንዚ-ማሊክ እዝያ ገዥ ተደረገ። ኢሻር-ዳሙ ካረፈ በኋላ ግን ምናልባት 2074 ዓክልበ. ግ. ሳርጎን ወይም ማሪ ኤብላን እንዳጠፋ ይመስላል።

ከዚህ በኋላ ኤብላ እንደገና እንደተሠራ ይታወቃል። በላጋሽ ንጉሥ ጉዴአ ዘመን (2009-1989 ዓክልበ.) በአንዱ ሰነድ ጉዴአ የአርዘ ሊባኖስን ዕንጨት ከኤብላ ግዛት ከኡርሹ ይጠይቃል። በኡር ንጉሥ አማር-ሲን ፯ኛው ዓመት (1912 ዓክልበ.) የኤብላ ንጉሥ ይጠቀሳል። ከዚህም በኋላ ኤብላ ሁለተኛ ምናልባትም በሑራውያን ዕጅ እንደ ጠፋ ይታሥባል።

ዳግመኛም ተሠርቶ በሦስተኛው የኤብላ መንግሥት ወቅት፣ የንጉሥ ኢቢት-ሊም ሐውልት ቅርስ ተገኝቷል፤ ልክ መቼ እንደ ነገሠ ግን ገና እርግጠኛ አይደለም። የኤብላ ንጉሥ ኢመያ በግብጽ ፈርዖን ሆተፒብሬ ዘመን (1806-1803) እንደ ገዛ ከአንድ ሐውልት ቅርስ ታውቋል። በያምኻድ መንግሥት ዘመን ለያምኻድ ተገዥ ነበረ፤ የአላላኽ ገዥ አሚታኩም ልጅ የኤብላን ልዕልት አገባ። የኬጥያውያን መንግሥት ንጉሥ 1 ሙርሲሊ በ1508 ዓክልበ. ግ. ኤብላንም ያምኻድንም አጠፋቸው። በዚያን ጊዜ የኤብላ መጨረሻ ንጉሥ ኢንዲሊማ ተባለ።

ከዚያ በኋላ በሥፍራው ላይ ጥቃቅን መንደር ብቻ ቀረ፣ ይህም ምናልባት እስከ 500 ዓ.ም. አካባቢ ድረስ ቆየ።

Listed in the following categories:
አስተያየት ለጥፍ
ምክሮች እና ፍንጮች
ለ ኤብላ ገና ምንም ምክሮች ወይም ፍንጮች የሉም። ምናልባት ለእርስዎ ተጓlersች ጠቃሚ መረጃዎችን ለመለጠፍ እርስዎ የመጀመሪያ ሊሆኑ ይችላሉ? :)
DoubleTree by Hilton Van

$50 ጀምሮ

Elite World Van Hotel

$71 ጀምሮ

Qafqaz Sahil Hotel

$35 ጀምሮ

Hyatt Place Jermuk

$111 ጀምሮ

Yegevnut Hotel

$37 ጀምሮ

Jermuk Ararat Health SPA

$87 ጀምሮ

በአቅራቢያ የሚመከሩ ዕይታዎች

ሁሉንም ተመልከት ሁሉንም ተመልከት
የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Bourzey castle

Bourzey castle is called also Mirza castle, (Arabic قلعة مير

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Al-Halawiyah Madrasa

Al-Halawiyah Madrasa (Arabic: المدرسة الحلاوية‎) is a madrasah complex

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Citadel of Aleppo

The Citadel of Aleppo (العربية. قلعة حلب) is a large medieval fort

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Junblatt Palace

Junblatt Palace (العربية. 'قصر جنبلاط'); originally Janpolad Palace

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Church of Saint Simeon Stylites

The Church of Saint Simeon Stylites (Arabic: كنيسة مار سمعان ا

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Qasr ibn Wardan

Qasr ibn Wardan (قصر أبن وردان in Arabic) is a 6th century castle com

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Shaizar

Shaizar, Shayzar or Saijar was a medieval town and fortress in Syria,

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Sabkhat al-Jabbul

Sabkhat al-Jabbūl or Mamlahat al-Jabbūl or Lake Jabbūl (Arabic: سب

ተመሳሳይ የቱሪስት መስህቦች

ሁሉንም ተመልከት ሁሉንም ተመልከት
የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
ማቹ ፒቹ

ማቹ ፒቹ በፔሩ አንዴስ ተራሮች መካከል የሚገኝ የቀድሞ ከተማ እና የአሁን ፍርስራሽ ነው።

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
አክሮፖሊስ

አክሮፖሊስ (ከግሪክ ακρος ከፍተኛ፣ πόλις ከተማ) ማለት በትርጉሙ 'ከፍተኛ ከተማ' ነው። ከሁሉ ታዋቂ የ

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Persepolis

Persepolis (Шаблон:Audio Old Persian: Pārsa, Modern Persian: تخت جم

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Quebrada de Humahuaca

The Quebrada de Humahuaca is a narrow mountain valley located in the

የምኞት ዝርዝርዎ ውስጥ ይጨምሩ
እኔ እዚህ ነበርኩ
ጎብኝተዋል
Pompeii

Pompeii was an ancient Roman town-city near modern Naples, in the

ሁሉንም ተመሳሳይ ቦታዎች ይመልከቱ